ግንቦት 12, 2026

የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም ያለፈው አፈጻጸም  ተገምግሟል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (ከመልሚ)  በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም የክሎሎችና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር  የ2018 በጀት ዓመት  የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም በፕሮጀክቱ ባለሙያዎች ቀርቦ  ተገምግሟል፡፡

ፕሮጀክቱ የገጠሩን አከባቢ የትምህርት፣ የጤና፣ የግብርና ዕድገትና ተደራሽነትን በማሳደግ በአከባቢው ያለውን ማህበራዊ መስተጋብር  በማሳለጥ ረገድ ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው  ተናግረዋል፡፡

ፕሮጃክቱ በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግስት አጋርነት የሚተገባረው  ውጤታማ እንዲሆን የባለሙያ ቅንጅት ብሎም የአመራሩ ቁርጠኝነት በእጅጉ እንደሚያስፈልግ የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም ፕ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድ አሚን ገልጸዋል፡፡ 

በመጨራሻም ለፕሮጀክቱ አጋዥ የሆኑ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች (ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተር፣ ላብቶፕ ፣ ታብሌት፣ ፕሪንተርና መሰል ዕቃዎች) በክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ለክልሎችና ለከተማ አስተዳሩ ተበርክቷል፡፡

Posted in: ዜና