ነሐሴ 17, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም (ከመልሚ)“ዴይላይት ኢንተርናሽናል” በተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት የተጠና የግዥ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት የመጀመሪያ ረቂቅ ለከተማና መሠረተ-ልማት ዘርፍ አመራሮችና በግዥና ፋይናንስ ስራ ላይ ለተሰማሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ነው የቀረበው፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ አዳራሽ የቀረበው የዳሰሳ ጥናት የግዥ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያስችል  ለሚደረግ የምክክር መድረክ ተጨማሪ ግብኣትን ለመሰብሰብና ጥናቱን በተሟላ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ግብኣትን ለማግኘትና ማስተካከያዎችን ለማድረግ ዓላማ ያደረገ ሲሆን መድረኩ በክቡር ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የተመራ ነው፡፡

ረቂቅ ጥናቱን ያቀረቡት የጥናት ቡድኑ አማካሪዎች የሄዱበትን ርቀትና ከዘርፉ ተቋማት የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመገናኘት ባገኙት መረጃ መነሻነትና በቃለ-መጠይቅ ያገኙትን መረጃ ወስደው በተቀመጠው የጥናት ሥነ-ዘዴ በመመስረት ተቋማት ግዥን በቴክኖሎጂ ታግዘው በመፈጸምና የፋይናንስ አስተዳደርን በተገቢው መንገድ በመምራት የተመደበን በጀት ለታለመለት ዓላማ ብቻ ማዋል በሚቻልበትና የግልጽነትና የተጠያቂነት አሠራርን ዕውን ለማድረግ በመንግስት በኩል ያለውን ተነሳሽነት ወደ ተጨባጭ እውነት ለመቀየር እንዲያስችል ታልሞ እየተጠና ያለ ጥናት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

Posted in: ዜና