General Background General Background
Minimize Maximize

 

የወሊሶ ከተማ መልከኣ ምድራዊ አቀማመጥና የአየር ንብረቷ

የወሊሶ ከተማ መልከኣ ምድራዊ አቀማመጥ 95 በመቶ ሜዳማ ነው፡፡ ከተማዋ ተፈጥሮ በለገሳት ለጥ ያለ ሜዳ ላይ ወደ አራቱም አቅጣጫ እየደገች የሚትገኝ ሲሆን በሰሜን ምስራቅ በኩል በወሊሶ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ኮረብታማ የመሬት አቀማመጥ የከተማዋ እይታ ልዩ ውበት እንድኖራት አድርጎታል፡፡ ወሊሶ ከተማ  በአስትሮኖሚ እይታ በሰሜን 8031’ 47’’ ፣በምስራቅ 37058’ 59’’ እንድሁም በሰሜን 8031’ 59’’ ላቲቱድና በምስራቅ 37058’ 59’’ ሎንግቲድ ላይ ትገኛለች፡፡ የወሊሶ ከተማ ከባህር  ጠለል በላይ በ1900 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች፡፡ የአየር ንብረቷ ወይና ዳጋ ስሆን አመታዊ  የሙቀት መጠኑም ዝቅተኛ 18 ዲ.ሴ.ግ ከፍተኛው 27 ዲ.ሴ.ግ በመሆኑ ወሊሶ ለኑሮም ሆነ ለሥራ በጣም ተስማሚ ናት፡፡ የዝናብ መጠን በአማካይ 1200 ሚ/ሊትር ነው፡፡ በዓመት ከ7 ወራት ያላነሱ ጊዜ ዝናብ የሚታገኝ አካባቢ በመሆኗ ዙሪያዋ በዝናብና በመስኖ የሚለማና አመቱን በሙሉ አትክልት፣ ፍራፈሬና የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለገበያ እያቀረበች ትገኛለች፡፡ ከተማዋ ክረምት ከበጋ የሚፈሱ ሦስት ወንዞች መካከል መገኘቷ  ልዩ ያደርጋታል፡፡ እነዚህ ወንዞች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ወሊሶ ከተማ ባላት ምቹ ሁኔታ የብሔር ብሔረሰቦች የመኖሪያ ስፍራም ሆናለች፡፡ በአሁኑ ወቅት የነዋሪዎቿ ቁጥር ከ54,000 በላይ የደረሱ ስሆን በዕለት ዕለት እንቅስቃሴ በአራቱም የመግቢያና መውጫ በሮችዋ ወደከተማው የሚመጣዉ የህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ በከተማው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲመጣ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡