Web Content Display Web Content Display
Minimize Maximize

የሀደሮ ከተማ ፊዝካላዊና ማህበራዊ መረጀ

የሀደሮ ከተማ የተመሠረተችበት ዘመን፡-

የሀደሮ ከተማ መጀመሪያ የተመሠረተችዉ በቀዳማዊ አጼ /ሥላሴ ዘመነ መንግስት 1943 /ም፣ ሲሆን ህጋዊ ዕዉቅና ያገኘችበት 1985 /ም፣ በታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የተመዘገበችዉ 1994 /ም፣ ወደ ከተማ አስተዳደር የተሸጋገረችበት 2007 / ነዉ፡፡

የሀደሮ ከተማ መገ ቦታ፡- በደቡብ ከልላዊ መንግሥት፣ከምባታ ጠምባሮ ዞን፣ሀደሮ ከተማ አስተዳደር፤ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በሆሳዕና በኩል 295 ኪ/ሜ፤ከሀዋሳ በስተሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ 150 ኪ/ሜ፤ከዱራሜ ከተማ በስተምዕራብ 31 ኪ/ሜ ላይ ትገኛለች፡፡

የሀደሮ ከተማ ዓመታዊ የአየር ፀባይ ሁኔታ፡-ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን 1500 ሚ/ሜዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠን ዝቅተኛ 15 ድ/ሴ ከፍተኛ 27 ድ/ሴከፍታ ከባህር ጠለል በላይ በአማካይ 1560 ሜትር ሲሆን የመሬት አቀማመጧም በሁሉም አቅጣጫ ለጥ ያለ ሜዳማ በመሆኑ ለኑሮ እጅግ ተስማሚና ተመራጭ ያደርጋታል፡፡

የሀደሮ ከተማ ህዝብ ቁጥር በተመለከተ፡-1999 ዓ/ም የኢትዮጵያ የህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ መሠረት የሀደሮ ከተማ ህዝብ ብዛት ወንድ 24,916 ሴት 25,021 ድምር 49,937 የህዝብም አመታዊ እድገቱ በፐርሰንት 5.4 %ነው፡፡

የሀደሮ ከተማ አደረጃጀትና መዋቅር በተመለከተ፡- በአራት የቀበሌ አስተዳደር መዋቅር ስር ትተዳደራለች፡፡በከተማዋ የሚገኙ ቅርሶችና መስህቦች በተመለከተ፡-ከተማዋ በሳና፣በዶጄ እና በሶኬ ወንዞች የተከበበች መሆኗና ወንዞቹም ክረምት ከበጋ መፍሰሳቸዉ የከተማዋን ልምላሜ ከማረጋገጡም በላይ ከዓመት ዓመት የፍራፍሬና አትክልት መገኛ ደሴት ያደርጋታል፡፡በከተማዋ ጥግ የሶኬ ፏፏቴና ከከተማዋ ትንሽ ወጣ ብሎ የአጆራ መንትያ ፏፏቴዎች መገኛ መሆኗ ለመስህብነት አድሏታል፡፡

ከተማዋ ለኢንቨስትመንት ምቹ ስለመሆንዋ፡-የሰዉ ጉልበት በተፈለገዉ ያህልና በተመጣጣኝ ዋጋ ከመገኘቱም በላይ ከተማዋ ለጥ ያለ( ሜዳማ) አቀማመጥ ያላት መሆኑ በየትኛዉም የቀበሌ ጫፍ ላይ የፈለጉትን ዓይነት ኢንቨስትመንት ለማልማት በቂና ምቹ ከተማ መሆንዋ ተፈላጊ ያደርጋታል፡፡ከጥሬ ሀብት አቅርቦት አንፃርም የግንባታ ቁሳቁሶች  ድንጋይ፣አሸዋ፣እንጨት፣ዉሃ…ወዘተ) የመሳሰሉት በቅርብ ርቀት ከተማዋን በከበቡት ወንዞች ዙሪያ መገኘቱ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል፡፡ከተማዋና የከተማዋ አጎራባች ቀበሌያት በዝንጅብል፣በቡና ምርት እና በፍራፍሬ (ሙዝ፣ አቦካዶ፣መንጎ፣ፓፓዬ…ወዘተ በቂና ከበቂ በላይ የሚመረትባት ከተማ መሆንዋ፡፡

የትራንስፖርት ተደራሽነትን በተመለከተ፡-ከዱራሜ ሙዱላ - ዱርጊ አስፋልት መንገድ የሀደሮን ከተማ ለሁለት ከፍሎ የሚያልፍ መሆኑ

ከአዲስ አበባ በሆሳእና ወላይታ ሶዶ የሚያልፈዉ አስፋልት መንገድ በ6 ኪ/ሜ ርቀት በስተምስራቅ ሌሾ ማዞሪያ ከተማን አቋርጦ የሚያልፈዉ አስፋልት መንገድ በቅርብ ርቀት መኖሩ እናበተጨማሪም የገጠር ከተሞችንና ቀበሌያትን የሚያገናኝ በገጠር መንገድ ፕሮጀክት( ዩራፕ) የተገነቡ፣ ከከተማዉ እስከ አጆራ ፏፏቴ፣ከከተማዉ እስከ ሶኬ ፏፏቴ፣ከከተማዉ እስከ ላሎ፣ከከተማዉ እስከ ፌሌዕቾ እንዲሁም ከከተማዉ እስከ ወላይታ ዞን ጥዮ፣ህምቤቾና ቦመቤ የሚያገናኝ የፕስታ መንገድ መገንባቱ እና የከተማዉ የወስጥ ለዉስጥ መንገድ በኮብልስቶን ንጣፍ ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ እስከአሁን  በየዓመቱ ሳይቋረጥ መገንባቱ ለትራንስፖርት ምቹ እና ተመራጭ እያደረጋት መጥቷል፡፡

            

        የሀደሮ ከተማ ፊዝካላዊና ማህበራዊ መረጀ