Home Home
Minimize Maximize

 

የሾኔ ከተማ አስተዳደር

የሾኔ ከተማ ከመቆርቆሯ በፊት አሁን ያለችበት ቦታ ለግብርና አገልግሎት ይውል እንደነበር የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡በወቅቱ የአርብ ገበያ ቦታ “ሰጋር” ሜራ በሚል ስያሜ ተቋቋመ፡፡ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኃለ ሰጋር ሜራ፤“ላሎ” ሜራ በሚል ስያሜ ከተቀየረ በኃላ ሳይቆይ “ሾኔ” በማለት የተቀየረ ሲሆን ትርጉሙም “አይግደል” ማለት እንደሆነም የዕድሜ ባለፀጎች ይናገራሉ፡፡የሾኔ ከተማ የምስራቅ ባደዋቾ ወረዳ ዋና ከተማ ተብሎ ከሚጠራበት ወደ ከተማ አስተዳደርነት ተፈቅዶ እንዲቀየር በክልል ደረጃ የፀደቀው መጋቢት 30/2007 ዓ/ም ሲሆን ወደ ሥራ የገባበት ጊዜ ግን ጥቅምት 20/2008 ዓ/ም ነው፡፡ከተማው በሁለት ክፍለ ከተማ በመከፋፈል ማለትም አረንቻና ሊቻ በማለት በስሩ ስድስት ቀበሌዎችን ያቀፈ እንዲሆን ተደርጓል፡ከዝህ በኃላ የተለያዩ መዋቅሮች ከለይ ወደ ታች እየወረደ ተግባረዊ እየሆነና ሴክተር መስሪያ ቤቶች እየተፈቀደ ሥራዎችን ኢያከነወነ ይገኛል፡፡

            የከተማዋ ቶፖግራፊ

 የሾኔ ከተማ መልካዓም ምድረዊ አቀመማጥ ፡-በ06077 North latitude እና 37070 East 380 ነው፡፡ከባህር ጠለል ከ1000 ሚ.ሜ እስከ 2500 ሚ.ሜ ከፍታ በላይ ትገኛለች፡፡ለጥ ያለ የመሬት አቀማመጥ አላት፡፡

ምቹ አጋጣሚዎች

ምቹ የአየር ንብረት ያላትና ለመኖሪያ እና ለእንቨስትመንት ከተማ አመቺ መሆኑ፤ለጥ ያለ ሜዳማ መልከ-ዓምድር መኖሩ በአቅራቢያዉ የቱሪስት መስቦች መኖራቸዉ ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ ከተማ ያደርጋታል፡፡ ለአብነትም፡-ቡዳ አመዳ፤ጥዕሎ፤መጨፈራ ሀይቆች እና አደቤ ፍል ዉሃ፤ሻላ ቦሎ ዋሻ፤ፊንጫዋ ፏፏቴ፤ጃርሶ ቁጡቤ ተክል ድንጋይ፤የአህመድ ግራኝ ተክል ድንጋይ፤የሾኔ እንግዴ ዳገት እና ትልቁ የአርብ ገበያ አገበያየት ስርዓቱ ታሪካዊና አንጋፋ መሆኑ እንዲሁም የሾኔ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጥንታዊነት ያለዉ መሆኑ….ወዘተ ናቸዉ፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት መስህቦች መካከል 3ቱ ሀይቆች በክልሉ ፍኖተ ካርታ የተመዘገቡ ሲሆን የሾኔ ከተማ የነዚህ የቱሪስት መስህቦች መዳረሻ ከተማ ተብላ ተመዝግባለች ፡፡

የአየር ፀባይ

85%የሚሆን ወይነ ደጋ ነው፡፡በዓመት በአማካይ የዝናብ መጠን ከ601 ሚ.ሜ እስከ 1600 ሚ.ሜ ይደርሳል፡፡

የተፈጥሮ ዕጽዋት

ዋርካ፤ባህር ዛፍ፣ዝግባ፣ጥድ፣ዋንዛ፣ግራቪሊና የመሳሰሉትም ይገኙበታል፡፡

በአከባቢዉ የሚመረቱና ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶችና ወደ ዉጪ የሚላኩ ምርቶች

ጤፍ፤በቆሎ፤ቀይ ቦሎቄ፤ቡና፤ሸንኮራ አገዳ፤ጫት፤ሙዝ፣አቮካዶ እና የተለያዩ ፍራፍሬዎች የሚመረቱ ሲሆን ከከተማችን ወደ ዉጪ የሚላኩ (ቀይ ቦሎቄ ሲሆን)ተጨማሪ ባለሀብቶች ቢሰማሩ ዉጤታማ ስለሚሆኑ ከተማዉ ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ያሳዉቃል፡፡

የሾኔ ከተማ አቀማመጥ

ከአድስ አበበ 345 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፣ከሀዋሳ በ120 ኪ.ሜ ትገኛለች፣ከሆሳዕና (ከዞኑ ርዕሰ ከተማ) በ95 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፣ከሻሸመኔ በ90 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፣ከወለይታ ሶዶ በ38 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች

የከተማ ህዝብ ብዘት

አጠቃለይ የህዝብ ብዛት 85000 ሲሆን ወንድ 35000 ሴት 50000 ነው፡፡የህዝብ ጥግግት 461 በካሬ ሜትር ስኩየር፡፡ከአጠቀለይ ህዝብ ብዛት ዕድሜያቸው ከ 15 እስካ 64 ያሉት ወደ 72.4% የሚሸፍን ሲሆን ቀሪው 27.6%  ከ0 እሰካ 14 እና 65 ዕድሜ ውስጥ ያሉትን ይወክለል፡፡ይህ የሚያሰየው የከተማዋ 72.4% አምራቹ ዜጋ እንደሆነ ነው፡፡

Pages: 1  2